የመማር ልምድን መቅረጽ

ሠልጣኞች ሁሉ ወይም የታሰቡት ውጤቶች አንድ ዓይነት እንደማይሆኑ በመገንዘብ ይህ የትምህርትና የሥልጠና መመሪያ ከፍተኛ ተለዋዋጭነትን ግምት ውስጥ በማስገባት ተዘጋጅቶአል፡፡ ዓላማው በውጤታማ ሕግ አማካይነት እኩል የሥራ ዕድሎችን ለአካል ጉዳተኞች ለማስፋፋትና ለማሳደግ ሆኖ ሳለ ይህ የሚከናወንባቸው መንገዶች ይለያያሉ፡፡ መመሪያው በሦስት መርሆዎች ላይ የተመሠረተ ነው፡-

  • እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን ለአካል ጉዳተኞች ለማስገኘት ተጽእኖ ለማድረግ በቁልፍ ቦታዎች የሚገኙ ግለሰቦች ያንን ግብ ለመምታት አንድ የተወሰነ እውቀት፣ ሙያዎችና ስልቶች ሊኖሩአቸው ይገባል፡፡
  • በውሱንና ልዩ ፍላጎቶቻቸው ላይ ተመሥርቶ ለእነዚህ ግለሰቦች መረጃ መስጠት፡፡  ለአንድ ፖሊሲ አውጪ ከሚሰጠው በተቃራኒ ለአንድ ዋና ተሟጋች የሚሰጠው መረጃ ተመሳሳይ ለውጥ ሊያስገኝ፣ በአመለካከቶቻቸውም ላይ ተመርኩዞ ሊለያይ ይችላል፡፡ ዋና ተሟጋቹ ፖሊሲዎቹ እንዴት እንደ ወጡ መግለጫ ሊፈልግ ሲችል የፖሊሲ አውጪው በዚህ መስክ አስቀድሞ ጥልቅ እውቀት ያለው፣ ግን ደግሞ የአካል ጉዳት መብቶች ጉዳዮች ዙሪያ መሠረታዊ ግንዛቤ ላይኖረው ይችላል፡፡
  • ለኮርስ ተሳታፊው ለውጡን ለማሳደግ ተጨማሪ አገር ነክና ለአካባቢ አግባብነት ያላቸው ምሳሌዎችና መረጃ ያስፈልጋሉ፡፡

እያንዳንዱ ክፍለ ትምህርት እነዚህን መርሆዎች በመደገፍ የዘዴዎችን ስብስብ ያቀርባል፡፡ ለእያንዳንዱ ክፍለ ትምህርት መሠረታዊ የዋነኛ ሥልጠና ዝርዝር ይሰጣል፡፡ ሙሉውን የዋነኛ ሥልጠና ዝርዝር ለማጠናቀቅ ከ30 እስከ 40 ሰዓታት የሚጠይቅ ሲሆን በሠልጣኞቹና በታሰበው ውጤት ላይ በመመርኰዝ ከአራት እስከ አምስት ቀኖችን በሚሸፍን ቀጣይ የትምህርት መልክ፣ ወይም በአንድ የተወሰነ ጊዜ በሚደረጉ ተከታታይ የብዙ ሰዓት ዝግጅቶች ሊካሄዱ ይችላሉ፡፡ እያንዳንዱ ዋነኛ የሥልጠና ዝርዝር፣ ምክንያት፣ የመማር ዓላማዎች፣ ቆይታ፣ ቁልፍ ጽንሰ ሃሳቦች፣ አዘውትሮ የሚያገለግሉ ቃላትና ሃሳቦች መፍቻን ይሰጣል (አባሪ ሀ)፡፡ የመማር ልምዱን ለማሳደግ አስፈላጊ የሆኑ ጽንሰ ሃሳቦችን መመሪያ ለመግለጽና ሙከራን ለማስቻል በሥልጠናው ዝርዝር ሁሉ አማራጭ መልመጃዎች ቀርበዋል፡፡ ይህ የተስፋፋ የመማር አማራጭ ተጨማሪ መልመጃዎችን፣ የሙከራ ልምዶችን፣ እንዲሁም የትምህርት አሰጣጥ ጽሁፎችን ይሰጣል፡፡ በመጨረሻም እያንዳንዱ ክፍለ ትምህርት ናሙና አስተያየቶችን/የግምገማ መገልገያዎችን፣ የኢንተርኔት ምንጮችን፣ እንዲሁም ማጣቀሻዎችንና ሊነበቡ የሚያስፈልጉ ጽሁፎችን ይጠቁማል፡፡ ከታች የሚታየው የቁልፍ ሥዕሎች መግለጫ የእንዳንዱን ክፍለ ትምህርት አቀማመጥ ሲሰጥ በማሠልጠኑ ሂደት የሚያገለግሉ ምስሎችን ያሳያል፡፡

  • የመማር ዓላማዎች
  • የጊዜ ገደብ
  • ቁልፍ ሃሳቦች
  • የቃላት መፍቻ
  • የሥልጠና ዝርዝር
  • አጀማመር
  • አማራጭ መልመጃዎች
  • የግምገማ ውጤት
  • የኢንተርኔት ምንጮች
  • ማጣቀሻዎችና ንባቦች
  • አባሪ
  • የገለጻ ማሳያዎች