ይህ ክፍለ ትምህርት ይህን መመሪያ በመጠቀም ረገድ የመማርን ልምድና በሕግ አማካይነት ለአካል ጉዳተኞች እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን በማስከበር ዙሪያ ሊከሰት የሚችል ውጤትን ለማሳደግ ጠቃሚ ምክሮች ይሰጣል፡፡

ይህ ክፍለ ትምህርት የአካል ጉዳትን፣ የመድልዎ አልባነትና የእኩልነት መርሆን፣ በሕግ ውስጥ የአካል ጉዳትን ጭብጥ፣ እንዲሁም ወደ አዎንታዊ እርምጃ የሚያመራ ማኅበራዊ ፖሊሲን በመዳሰስ ረገድ ሠልጣኙን በመርዳት አካል ጉዳትን እንደ ሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ያረጋግጣል፡፡

ይህ ክፍለ ትምህርት የመድልዎ አልባ ሕግን ጠቀሜታ በአጽንኦት የሚያሳይ ሲሆን የአካል ጉዳት ሕግ መያዝ ያለበትን አድማስ በአጭሩ ያትታል፡፡ በተጨማሪም ይህ ክፍለ ትምህርት ሊከሰቱ የሚችሉ የመድልዎ ዓይነቶችን አጉልቶ የሚያሳይ ሲሆን ለተመጣጣኝ ማመቻቸት አስፈላጊነት ጭብጥን ይመሠርታል፡፡

ይህ ክፍለ ትምህርት የኮታ ቀረጥ ዘዴ ምን እንደ ሆነና ውጤታማ ማበረታቻ ሳይኖር ለአስገዳጅ ኮታ ተገቢ የሆኑ ጉዳዮችን በመሸፈን የኮታ ዘዴዎችን አጠቃላይ እይታ ይሰጣል፡፡ የኮታ አሠራሮች በተግባር እንዲሠሩ የሚያደርጉ ተግባራዊ ስልቶች ጐልተው ተቀምጠዋል፡፡

ይህ ክፍለ ትምህርት አንድ አገር የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕግ ለመተግበር በሚያቅድበት ጊዜ መጤን ያለባቸውን አስፈላጊ ነጥቦች ይዘረዝራል፡፡ ይዘቱ በመረጃ ዘመቻዎች ሚና፣ የሕጉን ትግበራ ለመደገፍ ጥበቃ ለሚደረግለት የአካል ጉዳተኞች ሁኔታ እና/ወይም ለድርጅቶችና ለአሠሪዎች ሊሰጡ በሚችሉ ወሳኝ የሥራ ስምሪት ድጋፍ እርምጃዎች ዙሪያ ውይይት ያካትታል፡፡

ይህ ክፍል ውጤታማ የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕግ በማውጣት ረገድ ምክር ሊጠየቁና ኃላፊነቱ ሊሰጣቸው ከሚገባው ባለ ድርሻዎች ጋር ግንኙነት ላላቸው ፖሊሲና ሕግ አውጪዎች አጠቃላይ መመሪያ ይሰጣል፡፡ አካል ጉዳተኞችና የሚወክሉአቸውን ድርጅቶች፣ አሠሪዎችና የአሠሪዎችና ማኅበራትን፣ ሠራተኞችና የሠራተኛ ማኅበራትን፣ አገልግሎት ሰጪዎችና ፍላጎቱ ያላቸውን ሌሎች ወገኖች ጨምሮ የተለያዩ ባለ ድርሻ ወገኖች ጠቅላላ እይታ ድጋፋቸውንና ተሳትፎአቸውን ለማግኘት ከሚጠቅሙ ስትራቴጂዎች ጋር ቀርቦአል፡፡ የምክክር ሂደቱ እንዴት መዋቀር እንዳለበትና ሌሎች አገሮች አስቀድሞ ሂደቱን እንዴት እንደ ቀረጹ ልዩ ምሳሌዎች ቀርበዋል፡፡

ይህ የመጨረሻ ክፍለ ትምህርት ሕግ በመረቀቅ ደረጃ ላይ እያለ ሕጎችና ፖሊሲዎች ተፈጻሚ የሚሆኑባቸውን መንገዶች ስለ ማቀድ አስፈላጊነት አጽንኦት ይሰጣል፡፡ ይህ ሕጎቹና ፖሊሲዎቹ በተግባር ምን እንደሚመስሉና መብቶች እንዴት እንደሚረጋገጡ መመልከትን ይጠይቃል፡፡ የውል ተገዢነትን እንደ መሳሰሉት ሌሎች አቀራረቦች ሁሉ ፍትሐዊ አሠራሮችን እንዲሁም አስተዳደራዊ አስፈጻሚ ተቅዋሞችን ለማጠናከር የሚወጡ ስትራቴጂዎችን ይመረመራሉ፡፡